ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
ሀገር ቤት ሚዲያ ኢትዮጵያዊ ይዘቶችን ማለትም ሲትኮሞችን፣ ተከታታይ ድራማዎችን፣ የተውኔት ፊልሞችን፣ ስታንድ አፕ ቀልዶችን፣ አጫጭር ፊልሞችን፣ አጫጭር ቪዲዮዎችን፣ የምግብ ዝግጅት ክፍለ-ጊዜዎችን እና የህፃናት አኒሜሽን ፊልሞችን በአማርኛ የሚያቀርብ በደንበኝነት ምዝገባ ላይ የተመሰረተ ዲጂታል መዝናኛ መድረክ ነው ። ይዘቶቻችን በሀገር ቤት ሚዲያ የተዘጋጁ ወይም ከኢትዮጵያውያን አዘጋጆች በብቸኝነት ፈቃድ የተገኙ ናቸው።
አዎ። ማንኛውም ያልተፈቀደ የመረጃ ፍስሰት እንዳይከሰት ደህንነትን ለማረጋገጥ የባንክ ደረጃ ያለው ኢንክሪፕሽን እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የክፍያ መተላለፊያዎችን (ጌትዌይስ) መጠቀማችን የክፍያ መረጃዎን ደህንነት ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ያደርገዋል። በመተግበሪያው ውስጥ ሁሉም ግዢዎች የሚከናወኑት በመተግበሪያ መደብር መለያዎ አቅራቢ በኩል ሲሆን፣ እሱም ጥብቅ የሆኑ ዓለም አቀፍ የክፍያ ደህንነት ደረጃዎችን ይከተላል። የካርድዎን ዝርዝር መረጃዎች በመረጃ ቋቶቻችን (ሰርቨሮቻችን) ላይ የማናከማች ከመሆኑም ሌላ እያንዳንዱ ክፍያ ከጫፍ እስከ ጫፍ የተመሰጠረ (ኢንክሪፕትድ) መሆኑ ገንዘብ-ነክ መረጃዎ ሚስጥራዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ እንደሚቆይ ሙሉ ማስተማመኛ ይሰጥዎታል።
በመተግበሪያው ውስጥ በውስጠ-መተግበሪያ ግዢ ይመዘገባሉ፤ ክፍያው የሚፈጸመው ከመተግበሪያ መደብር መለያዎ ጋር የተገናኘውን የክፍያ ዘዴ በመጠቀም ነው። ያሉዎት የክፍያ አማራጮች ክፍያ ከመፈጸምዎ በፊት በክፍያ ገጹ ላይ ይታያሉ።
አዎ። ተመዝጋቢዎችን ዘወትር ለማዝናናት መድረኩን በአዳዲስ ትዕይንቶች እና ፊልሞች ደጋግመን እናዘምነዋለን።
አዎ፣ በማንኛውም ጊዜ በመተግበሪያ መደብር መለያ ቅንብሮችዎ ውስጥ የደንበኝነት ምዝገባዎን መሰረዝ ይችላሉ።
አዎ። የሀገር ቤት ሚዲያ መለያዎች ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ አዋቂዎች ብቻ ናቸው። ልጆች ሊመለከቱ የሚችሉት በወላጅ ወይም በአሳዳጊ መለያ እና ቁጥጥር ስር ብቻ ነው። ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ ፕሮግራሞችን ጨምሮ ለተለያዩ ታዳሚዎች ተስማሚ የሆኑ ይዘቶችን እናቀርባለን።
በመተግበሪያው ወይም በድህረ-ገጹ ላይ ማንኛውም ችግር ካጋጠመዎት በመተግበሪያው ወይም በድህረ-ገጹ በኩል የድጋፍ ቡድናችንን በቀጥታ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ችግሮችን ለመፍታት ፈጣን እርዳታ እንሰጣለን።
መድረኩ አማርኛ እና እንግሊዝኛን የሚደግፍ ሲሆን፣ በመተግበሪያው እና በድህረ-ገጹ ላይ ቀላል የቋንቋ መቀያየሪያ አማራጭ ይገኛል።
የይዘቶች ክምችታችን የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦ • ፊቸር ፊልሞች • ሲትኮሞች • ተከታታይ ድራማዎች • አጫጭር ፊልሞች • ስታንድ-አፕ ቀልዶች • አጫጭር ቪዲዮዎች • የግጥም ምሽት • የምግብ ማብሰል ትዕይንቶች • የልጆች አኒሜሽን ፊልሞች በአማርኛ ይዘቶቻችን በሀገር ቤት ሚዲያ የተዘጋጁ ወይም ከኢትዮጵያውያን አዘጋጆች በብቸኝነት ፈቃድ የተገኙ ናቸው።
አዎ። እያንዳንዱ ዕቅድ መድረኩን በተመሳሳይ ጊዜ በበርካታ መሳሪያዎች ላይ እንዲመለከቱ ያስችልዎታል፦ የ1 ወር ዕቅድ እስከ 3፣ የ3 ወራት ዕቅድ እስከ 5፣ የ6 ወራት ዕቅድ እስከ 10 መሳሪያዎች።
ይግቡ ወይም መለያ ይፍጠሩ፣ ዕቅድ ይምረጡ እና ክፍያዎን ያረጋግጡ። በመተግበሪያው ውስጥ፣ በመተግበሪያ መደብር መለያዎ በውስጠ-መተግበሪያ ግዢ መመዝገብ ይችላሉ።
የ1 ወር፣ የ3 ወራት እና የ6 ወራት ዕቅዶች አሉን። ዋጋው እንደ መተግበሪያ መደብሩ እና እንደ ሀገሩ ይለያያል። ትክክለኛውን ዋጋ ከመመዝገብዎ በፊት በመተግበሪያው ውስጥ ያያሉ።
ሀገር ቤት ሚዲያ ከየትኛውም የአለም ክፍል የሚሰራ ሲሆን፣ ይህም ለኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንዲሁም በኢትዮጵያ ላሉ ተመልካቾች ተደራሽ ያደርገዋል።
ሀገር ቤት ሚዲያን በሁለት መንገድ መጠቀም ይችላሉ፦ • በሞባይል መተግበሪያ፦ ከመሳሪያዎ የመተግበሪያ መደብር ያውርዱ። • በድህረ ገጽ፦ በማንኛውም የላፕቶፕ ወይም የዴስክቶፕ ኮምፒውተር አሳሽ በኩል ተደራሽ ነው።
ሀገር ቤት ሚዲያ ኢትዮጵያዊ ይዘቶችን ማለትም ሲትኮሞችን፣ ተከታታይ ድራማዎችን፣ የተውኔት ፊልሞችን፣ ስታንድ አፕ ቀልዶችን፣ አጫጭር ፊልሞችን፣ አጫጭር ቪዲዮዎችን፣ የምግብ ዝግጅት ክፍለ-ጊዜዎችን እና የህፃናት አኒሜሽን ፊልሞችን በአማርኛ የሚያቀርብ በደንበኝነት ምዝገባ ላይ የተመሰረተ ዲጂታል መዝናኛ መድረክ ነው ። ይዘቶቻችን በሀገር ቤት ሚዲያ የተዘጋጁ ወይም ከኢትዮጵያውያን አዘጋጆች በብቸኝነት ፈቃድ የተገኙ ናቸው።